top of page

መረዳጃ ማህበር (እድር)

መረዳጃ ማህበር (ዕድር)

በሀገራችን በኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን እንደሚሰራበት የአንድ አካባቢ ነዋሪ ሕዝብ እርስበርሱ በማህበር (በዕድር) ተደራጅቶ በሞት ጊዜ ለቀብር ሲረዳዳ መቆየቱ ይታወሳል። እኛም በኮሎራዶ ስቴት በዴንቨር ከተማና አካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ -ኢትዮጵያውያን ይህንኑ የሀገራችንን የመረዳዳት መልካም ባህል በመከተል : የማሀበሩ አባል ወይም ቤተሰብ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የቀብር ሥነ-ስርዓት ወጪን ለመሸፈን የሚረዳ ቀጥሎ በተመለከተው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መረዳጃ ማህበር (ዕድር) አቋቁመናል

ዓላማው

ዓላማው ፦ አንድ አባል ወይም ቤተሰቡ  ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለቀብር  ማስፈፀሚያ ወይም አስከሬኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመላኪያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ በማድረግ እርስ በርስ ለመረዳዳት ነው።

ተልእኮው

አባላት  በቀብር ስነ ስርአት ላይ  እንዲገኙ፣ በባህላችን መሰረት ለቅሶ  በመድረስ እንዲያስተዛዝኑ  መንገርና ማስተባበር

Geda.jpg

Ethiopian Edir

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤ ትውልደ-ኢትዮጵያዊ ዕድሜው ከ18 አመት በላይ  የሆነ፤ በኮሎራዶ ስቴት በዴንቨር ከተማና አካባቢው ነዋሪ የሆነ፤ የማህበሩን መተዳደሪ ደንብ የተቀበለ፤ በፈቃደኝነት የማሀበሩ አባል ለመሆን ማመልከቻ ሞልቶ ያቀረበ ፣ማህበሩ የሃይማኖት ፤የዘር፤የፃታ፤ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳያደርግ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ በአባልነት ተቀብሎ ይመዘግባል ።

5፡2 የመረዳጃ ማህበሩ  አባል ለመሆን ፤ በኮሎራዶ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ድርጅት አባል መሆን  ጠቃሚና አስፈላጊም ነው።

bottom of page