top of page

መተዳደርያ-ደንብ

በሀገራችን በኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን እንደሚሰራበት የአንድ አካባቢ ነዋሪ ሕዝብ እርስበርሱ በማህበር(በዕድር) ተደራጅቶ በሞት ጊዜ ለቀብር ሲረዳዳ መቆየቱ ይታወሳል።እኛም በኮሎራዶ ስቴት በዴንቨር ከተማና አካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ -ኢትዮጵያውያን ይህንኑ የሀገራችንን የመረዳዳት መልካም ባህል በመከተል : የማሀበሩ አባል ወይም ቤተሰብ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የቀብር ሥነ-ስርዓት ወጪን ለመሸፈን የሚረዳ ቀጥሎ በተመለከተው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መረዳጃ ማህበር (ዕድር) አቋቁመናል።

መግቢያ፦

የማህበሩ አድራሻ በኮሎራዶ ስቴት በዴንቨር ከተማና አካባቢው ሲሆን ፤አድራሻው በኮሎራዶ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ጽህፈት ቤት የሚገኝበት 1540 S Havana St Suite 308 Aurora, CO 80012  ቢሮ ቁጥር 308 ነው።

አንቀጽ አንድ፦ መጠሪያ ስም

ማህበሩ በአሜሪካ የሀገር ውስጥ ገቢ ህግ (U.S.Internal Revenue Code 501 3 C ) ለትርፍ ያልተቋቋመ ፤ከማንኛውም ፖለቲካ ፤ ሃይማኖት ፤እና ዘር ገለልተኛ የሆነ ፤ ኢትዮጵያዊነትን ብቻ መሠረት ያደረገ ሲሆን ፤ ዓላማው ፦ አንድ አባል ወይም ቤተሰቡ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለቀብር ማስፈፀሚያ ወይም አስከሬኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመላኪያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ በማድረግ እርስ በርስ ለመረዳዳት ነው።

አንቀጽ ሶስት፦ ዓላማ

ልጆች ማለት፦ከአባሉ አብራክ የተወለዱ፤በህጋዊ ማደጎ ወይም ጉዲፈቻ የተገኙ ፤እድሜያቸው ከ18 አመት ያልበለጡ ወይም የኮሌጅ /ዩኒቨርሲት ተማሪ ሆነው እድሜያቸው ከ23 አመት ያልበለጡና፤ በወላጆች ድጋፍ አብሮ የሚኖሩ የጋራ ልጆች፤ የባል ወይም የሚስት ልጆች ወይም በህመም (በበሽታ) ምክንያት ወይም አካለ ስንኩል ሆነው የቤተሰብ ጥገኛ ሆነው እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ማለት ነው።

አንቀጽ አራት፦ ትርጔሜ

ቤተሰብ ማለት፦የማህበሩ አባል የሆኑ ባልና ሚስት ፤ እድሜያቸው ከ18 አመት ያልበለጡ ወይም በኮሌጅ/ በዩኒቭርሲቲ በመማር ላይ ያሉ እድሜያቸው ከ23 አመት ያልበለጡ) ፤በአባል ቤተሰብ የሚረዱና ከአባሉ ጋር የሚኖሩ ልጆች ማለት ነው።

አንቀጽ ስድስት ፦ መዋጮ ፤ግዴታና መብት፦

አንድ የመረዳጃ ማህበሩ አባል ለመሆን የሚፈልግ ሰው ለአባልነት የተዘጋጀውን ቅጽ ሞልቶ በመፈረም ያመለክታል።ባለትዳር ከሆኑና 18 ዓመት እድሜ ያልበለጡ ልጆቻቸውን በመዘርዘር ከባለቤቱ ጋር ቅጹን በመሙላትና በጋራ በመፈረም አባል ለመሆን ያመለክታሉ።

bottom of page