top of page

የእድር የአባልነት ክፍያዎን ለመክፈል በዓመት ሁለት ጊዜ የክፍያ ኢንቮይስ በሰጡን ኢሜል አማካኝነት ይላካል፡ የተላከለትዎን ኢንቮይስ ሊንክ ተጭነው የየወሩን የዓባልነት ክፍያ መክፈል የአባልነት ግዴታዎ ነው። ተጨማሪ መብትና ግዴታዎን ለማወቅ የእድሩን መተዳደርያ ደንብ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ክፍያዉ በአሥር ቀናት ዉስጥ ካልደረሰን፤ በመተዳደሪያ ደንባችን መሠረት
ተጨማሪ አሥር ቀናት በመስጠት፤ ከ25 ዶላር የመቀጫ ክፍያ መክፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በነዚህ ቀናቶች ዉስጥ ክፍያዉን ካልፈፀማችሁ፣ ከማህበሩ መሰናበትን እንደሚያስከትል
ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ የክፍያዉን አፈፃፀም ለማቃለል ይረዳ ዘንድ በስልክ ቴክስት
መላክ የጀመርን መሆኑን እየገለጽን፣ ክፍያውን በቀጥታ ከስልካችሁ ላይ
መክፈል የምትችሉ መሆኑንም እንገልጻለን፡፡

በኦንላይን መክፈል የማይችሉ ከሆነ የእድሩ ቢሮ

(1450 S Havana St Suite#308 Aurora, CO 80012)

ሶስተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 308 በአካል በመገኘት መክፈል ይችላሉ። ሁሉም የእድሩ አመራሮች በፈቃደኝነት የሚያገለግሉ በመሆናቸው ወደ ቢሮ የሚመጡ ከሆነ እባክዎን ቀደም ብለው ቀጠሮ እንዲይዙ እንመክራለን፤ እናመሠግናለን

የዕድር አባልነት ክፍያ

bottom of page